አዲስ ገጽ መጽሄት በኤድፋይ ህትመትና ማስታወቂያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር እየተዘጋጀች በየ15 ቀኑ ለንባብ የምትበቃ የግል ሚዲያ ውጤት ናት:: መሪ ቃላችን በሃሳብ ልዕልና እናምናለን!” የሚል ሲሆን ምክንያታችን ደግሞ ከፍ ያለ/የተሻለ/ ሃሳብ ምንጊዜም ቢሆን ለህዝቦች ኑሮ መሻሻል ጉልህ ሚና እንዳለው ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነው:: ታድያ ይህ ከፍ ያለ ሃሳብ ምንጩ ማኅበረሰባችን እንደሆነ ይታወቃል:: አዲስ ገጽ ደግሞ እንደ ነፃና ገለልተኛ የግል ሚዲያ እኒህ ሃሳባቸውን ለማካፈል ከተዘጋጁ ከማኅበረሰቡ የተወሰኑ ሰዎች እዕምሮ የሚፈልቁ ከፍ ያሉ ዘርፈ ብዙ ሃሳቦችን መልሳ ለብዙ ሚሊየኖች ለማቅረብ እየተጋች ያለች መጽሄት ናት::

መጽሄትዋ በሀገራችን መፍትሄ የሚሹ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጋ ከፍ ያሉ ሃሳቦችን ከማኅበረሰቡ ለማኅበረሰቡ ታደርሳለች:: ከሚዳሰሱ ጉዳዮች መካከል ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች፣ የፖለቲካ አስተሳሰቦች፣ መልክዐ-ምድርና የተፈጥሮ ሃብት ጉዳዮች፣ በአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ ያሉ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው፣ ፍልስፍና፣ ህግ፣ ታሪክ፣ አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ የሚነሱ ጉዳዮች፣ ስፖርትና ሌሎች መዝናኛዎቸ፣ ሞራልና ሥነ-ምግባር፣ ቴክኖሎጂ፣ ወዘተርፈ ይገኙበታል::

መጽሄትዋ ለማንኛውም ጥሩ ሃሳብ አልኝ ለሚል የማኅበረሰባችን አካል ክፍት ናትና እርስዎም እንደማኅበረሰብ አባልነትዎ ከላይ በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይም ሆነ ሌላ ላካፍለው የምችለው/የሚገባኝ/ ሃሳብ አልኝ የሚሉ ከሆነ እነሆ እድሉ አለዎት::

በሃሳብ ልዕልና እናምናለን!

አዲስ ገጽ መጽሄት

አዲስ አበባ