• የአዲስ ገጽ መጽሄት ድረ-ገጽ የቀደሙ እትሞችን በቀላሉ ለማንብ እንዲያስችል ሆኖ ተሻሻለ::

    የተከበራችሁ የአዲስ ገጽ መጽሄት ደንበኞች: እንደምታውቁት አዲስ ገጽ መጽሄት በቅርብ ለንባብ የበቃች የህትመት ሚዲያ ናት:: ድረ-ገጹን (www.addisgets.com) ጨምሮ ብዙ ነገሮችን ለማስተካከል እየተጋን እንገኛለን:: በዚህም የተነሳ ዌብ ሳይታችን ላይ በየቀኑ ለውጦች ይታያሉ:; ይህ ለውጥ የአንባቢዎቻችንን ፍላጎት ለማሟላት የምናደርገው ጥረት አካል ሆኖ እንዲታይልን በአክብሮት እንጠይቃለን:: አሁን በላው ድረ-ገጽ ላይ የቀደሙ ዕትሞችን ለማንበብ ሁለት አማራጮች አሉ:: “የዕትሞች ቋት” […]

  • መልካም የገና በዓል

    ለ“አዲስ ገጽ” መጽሄት አንባቢያን የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ   እንኳን ለ2008 ዓ.ም የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ::

  • ‹‹አዲስ ገጽ›› መጽሔት በድጋሚ ታትማ ነገ (ታህሳስ 26/2008 ዓ.ም) በገበያ ላይ ትውላለች

    ‹‹አዲስ ገጽ›› መጽሔት በድጋሚ ታትማ ነገ   በገበያ ላይ ትውላለች ———— ‹‹የአዲስ ገጽ›› መጽሄታችን አራተኛ ዕትም ባሳለፍነው ቅዳሜ ለንባብ መብቃቷ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን፣ በማተሚያ ቤት ዙሪያ በተፈጠረ ችግር የተነሳ፣ በአንባቢያን ዘንድ የአቅርቦት እና የፍላጎት አለመጣጣም ተከስቶ ነበር፡፡ ከቅዳሜ ዕለት አንስቶ እስከዛሬ ድረስ፣ መጽሔቷን ለማንበብ ፈልገው ገበያ ላይ ማጣታቸውን የገለጹልን በርካታ አንባቢን ነበሩ – ከአዲስ አበባ እና […]

  • የአዲስ ገጽ መጽሄት 4ኛ ዕትም ተጨማሪ 1500 ኮፒ

    ከብዙ አንባቢዎች በደረሰን ጥያቄ መሰረት የአዲስ ገጽ መጽሄት 4ኛ ዕትም ተጨማሪ 1500 ኮፒ ታትሞ ነገ ማክሰኞ ታህሳስ 26 ጠዋት ጀምሮ ለንባብ ይበቃል:: በተለይ አዲስ አበባ እና አካባቢው የምትኖሩ የቅዳሜው ዕትም ያለቀባችሁ አንባቢዎች “አዲስ ገጽ” ማከሰኞ በጠዋት እንገናኝ ትላችኋለች:: ቀጠዩን ዕትም በተቻለ መጠን በዛ ያለ ኮፒ ለማሳተም እንሞክራለን:: መጽሄታችንን መርጣችሁ ስለምታነቡ እናመሰግናለን::  

  • ‹‹አዲስ ገጽ›› መጽሄት አራተኛ ዕትሟ በነገው ዕለት(ታህሳስ 23/2008 ዓ.ም) ለንባብ ትበቃለች

    ‹‹አዲስ ገጽ›› መጽሄት አራተኛ ዕትሟ በነገው ዕለት  ለንባብ ትበቃለች፡፡ የተለያየ ፀሐፊያን ሀሳቦቻቸውን አቅርበዋል፡፡ በባለፈው ዕትም ሀሳባቸውን እንዲሰጡን ጠይቀናቸው በጊዜ አለመመቻቸት የተነሳ ሳይችሉ የቀሩት አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በዚህኛው ዕትም ስለተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ሀሳባቸውን በቃለ-ምልልስ መልክ ገልጸዋል፡፡ አቤ ቶኪቻውም በሽሙጡ ፈገግ አስደርጎናል፡፡ ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገ/ኪዳን ስር ስለሰደደው ሀገራዊ ሙስናና ስለመንግስት ኔትወርክ ምርጥ የሆነ ጽሑፉን አቅርቧል (በግሌ በጣም […]