‹‹አዲስ ገጽ›› መጽሔት በድጋሚ ታትማ ነገ   በገበያ ላይ ትውላለች
————

‹‹የአዲስ ገጽ›› መጽሄታችን አራተኛ ዕትም ባሳለፍነው ቅዳሜ ለንባብ መብቃቷ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን፣ በማተሚያ ቤት ዙሪያ በተፈጠረ ችግር የተነሳ፣ በአንባቢያን ዘንድ የአቅርቦት እና የፍላጎት አለመጣጣም ተከስቶ ነበር፡፡
ከቅዳሜ ዕለት አንስቶ እስከዛሬ ድረስ፣ መጽሔቷን ለማንበብ ፈልገው ገበያ ላይ ማጣታቸውን የገለጹልን በርካታ አንባቢን ነበሩ – ከአዲስ አበባ እና ከክልል ከተሞች፡፡
12 ብር ትሸጥ የነበረችዋን መጽሄትን ከ15-20 ብር ድረስ ለመግዛት የተገደዱም ሰዎች የገጠማቸውን ነግረውናል፡፡ በ5 ብር ተከራይው ያነበቡም ነበሩ፡፡

 

በመሆኑም የተከበሩ የ‹‹አዲስ ገጽ›› መጽሄት ቤተሰቦችንና አንባቢንን መሻት ለመሙላት፣ መጽሄቷን በድጋሚ ወደማሳተም አምርተናል፡፡ መጽሔቷም ነገ በድጋሚ ገበያ ስለምትውል፣ ያላገኛኋት አንባቢን ነገ እንድምታገኟት ስገልጽ ደስ እያለኝ ነው፡፡


በዚህ አጋጣሚ፣ ገንቢ እና አስተማሪ አስተያየት የሰጣችሁንን አንባቢያን ማመስገን

እፈልጋለሁ፡፡
መልካም ንባብ!

 

ኤልያስ ገብሩ

ዋና አዘጋጅ

 

 

About the author

Related Post

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *