ለተከበራችሁ የአዲስ ገጽ መጽሄት ደንበኞች:

በርካታ አንባቢዎች ድረ-ገጻችንን http://www.addisgets.com/ እየጎበኛችሁና እያነበባችሁ እንደሆነ እናውቃለን:: በድረ-ገጹ ላይ የመጽሄቱን ጽሁፎች የምናሰቀምጥበት ምክንያት በተቻለ መጠን ብዙ ወገኖቻችን እንዲያነቡት በማሰብ  ነው::  በድረ-ገጹ ላይ ያነበባችሁትንና የወደዳችሁትን ጽሁፍ እግረመንገዳችሁን ከእያንዳንዱ ጽሁፍ ስር ባለው የአስተያየት መስጫ ቦታ ሃሳባችሁን ብታስቀምጡ ለጻፉት ሰዎች ማበረታቻና ለሌሎች ወገኖችም ሃሳባችሁን ማካፈያ መንገድ ይሆናል::  በተጨማሪ እዛው ከእያንዳንዱ ጽሁፍ አጠገብ ባሉት አማራጮች በፌስቡክና ትዊተር እንዲሁም ጉግል+ ለሌሎች ወገኖች ሼር ብታደርጉ የተሻለ ቁጥር ባለው አንባቢ እንድንደርስ ትረዱናላችሁና የበኩላችሁን እንድትወጡ እንጠይቃለን::

በዚህ አጋጠሚ 9ኛ ዕትም በሚቀጥለው ቅዳሜ ለንባብ ትበቃለች ብለን እንጠብቃለን:: በጣም በጣም ሲፈታተነን የነበረውን የመጽሄት አከፋፋይ ችግር ባለፈው ሳምንት ለመፍታት ሞክረናል::  ይህንን ችግር ለመፍታት ስንል የህትመት ወቅታችንን መጠበቅ ባለመቻላችን ይቅርታ እንጠይቃለን:: በአዲስ መልኩ ተዘጋጅተን ለመቅረብም እየተጋን እንገኛለን::

ሳትሰለቹ እስካሁን ድረስ አብራችሁን ላላችሁ ጸሃፊያንና አንባቢዎች በሙሉ በጣም እናመሰግናለን::  አብረን የሀገራችንን ሚዲያ ለማጠናቀር እንስራ ፤ በመጽሄታችን ላይ በምናስተላልፈው መልዕክትም የሀሳብና የኑሮ ለውጥ ለወገኖቻችን ለማምጣት እንትጋ እንላለን::

በሃሳብ ልዕልና እናምናለን!

እናመሰግናለን::

 

 

About the author

Related Post

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *