የተከበራችሁ የአዲስ ገጽ ደንበኞች:

ምንም እንኳን ሙሉበሙሉ እየታገሉን ያሉ ችግሮችን መፍታት ባንችልም ቃላችንን ለመጠበቅ ያህል አዲስ ገጽ ተመልሳ መጥታለች:: በሂደት ሁሉም ተሰተካክሎ እነደምናይ ተስፋ እናደርጋለን::

ሌላው ነገር አዲስ ገጽ አሁን 13 ብር ሆናለች:: እንደምታውቁት በሀገራችን ባለው ሁኔታ የተነሳ ከሽያጭ ውጭ አዲስ ገጽ እራሷን የምትደጉምበት በቂ የማሰታወቂያ አማራጭ ለጊዜው የለም:: ድርጅቶችና ግለሰቦች መንግስታቸውንና ፖለቲካን እንደ መብት ማስከበሪያ ሳይሆን እንደጦር የሚፈሩባት ሀገር ሆናለች የኛዋ ኢዮጵያ:: ለመረጃ ያህል ማስታወቂያ ቀርቶ ማተሚያ ቤት እንኳን ለማግኘት ያሳለፍነውን መከራ መገለጽ ይከብዳል:: ከአዲስ ገጽ መጽሄት ጋር እንዲሰሩ የሚጠየቁ አካላት የሚሰጡትን ከፍርሃት ብዛት የተነሳ አሳዛኝና/ወይም አስቂኝ/ መልስ ለመግለጽ ቃላት በቂ አይደሉም:: የሰውነት እንቅስቃሴአቸውን አስቡት:: የሚገርም ነው:: እንግዲህ በዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ ውስጥ እያለፍን 1 ብር ጭማሪ ማድረጋችን ዘለቄታችንን ለማጠናከር ይረዳን ዘንድ ነውና አንባቢያን ቅር እንደማትሰኙብን እንተማመናለን::

ሌሎች ፈተና የሆኑብንን ጉዳዮች ለጊዜው ሳንገልጽ እንቀጥልና ቀኑ ሲደርስ እናጋራችሁዋለን::

አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስ ይለናል::
በሃሳብ ልዕልና እናምናለን!

እናመሰግናለን::

About the author

Related Post

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *