የተከበራችሁ የአዲስ ገጽ መጽሄት ደንበኞች:
እንደምታውቁት አዲስ ገጽ መጽሄት በቅርብ ለንባብ የበቃች የህትመት ሚዲያ ናት:: ድረ-ገጹን (www.addisgets.com) ጨምሮ ብዙ ነገሮችን ለማስተካከል እየተጋን እንገኛለን:: በዚህም የተነሳ ዌብ ሳይታችን ላይ በየቀኑ ለውጦች ይታያሉ:; ይህ ለውጥ የአንባቢዎቻችንን ፍላጎት ለማሟላት የምናደርገው ጥረት አካል ሆኖ እንዲታይልን በአክብሮት እንጠይቃለን::
አሁን በላው ድረ-ገጽ ላይ የቀደሙ ዕትሞችን ለማንበብ ሁለት አማራጮች አሉ::
- “የዕትሞች ቋት” የሚለውን ሜኑ ስትጫኑ ከዚህ በፊት ለንባብ የበቁት ዕትሞች ፊትለፊት ገፃቸው /ከቨር ፔጅ/ ይታያል:: ማንበብ የፈለጋችሁትን ዕትም የፊትለፊት ገጽ ስትጫኑ ወደሌላ ገጽ ይመራችሃል:: ከዚህ ገጽ ጀምሮ ገጽ በገጽ እዛው ለማንበብ በስተግራ ከታች በኩል ወደፊትና ወደ ኋላ ገጽ በገጽ ለመሄድ የሚያስችሉትን ቀስቶች በመጠቀም ማንበብ ትችላላችሁ ::
- ፒዲኤፍ ፋይሉን አውርዳችሁ ማንበብ ለምትፈልጉ ደግሞ “የዕትሞች ቋት” የሚለውን ሜኑ ስትጫኑ ከምታገኟቸው የቀደሙ ዕትሞች የፊትለፊት ገጾች ስር “Download PDF” የሚለውን በመጫን መጠቀም ትችላላችሁ::
እስተያየታችሁ አይለየን!
መልካም ንባብ::
Leave a comment