‹‹አዲስ ገጽ›› መጽሄት አራተኛ ዕትሟ በነገው ዕለት  ለንባብ ትበቃለች፡፡ የተለያየ ፀሐፊያን ሀሳቦቻቸውን አቅርበዋል፡፡ በባለፈው ዕትም ሀሳባቸውን እንዲሰጡን ጠይቀናቸው በጊዜ አለመመቻቸት የተነሳ ሳይችሉ የቀሩት አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በዚህኛው ዕትም ስለተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ሀሳባቸውን በቃለ-ምልልስ መልክ ገልጸዋል፡፡ አቤ ቶኪቻውም በሽሙጡ ፈገግ አስደርጎናል፡፡
ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገ/ኪዳን ስር ስለሰደደው ሀገራዊ ሙስናና ስለመንግስት ኔትወርክ ምርጥ የሆነ ጽሑፉን አቅርቧል (በግሌ በጣም ወድጄዋለሁ)፡፡ ሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ሥለአረብ ሀገራት የሥራ ሂደት አዋጅ መመሪያን በምክንያት እየተቸ ሀታታዊ ጽሑፍን ጀባ ብሎናል፡፡ ‹‹መባ›› ፊልምን መነሻ በማድረግ ግላዊ ሂሱን በማቅረብም በሀገራችን ስለሚገኙ የለአዕምሮ ሕሙማን ጥሩ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሀሳቡን በአዝናኝ መልኩ ያቀረበልን ደግሞ ዩሐንስ ሞላ ነው፡፡ ጋዜጠኛ እና ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉም ‹‹ሀሳብን የመግለጽ መብት ካላበሳጨ …››እያለን ነው፡፡ …
ቅዳሜን ‹‹አዲስ ገጽ››ን በማንበብ ያሳልፉ ስል ግብዣዬን አቅርቤያለሁ፡፡ ደግሞም ‹‹ሀሳብ አለን›› የምትሉ ወገኖች ሳትፈሩ ሀሳቦቻችሁን ግለጹ! በሀሳብ ሙግት እናድጋለን፣ በሀሳብ ልዕልና እንበለጽጋለን!!!

About the author

Related Post

2 Comments

  1. Giftu

    You guys are speaking the truth!!!!
    Keep it up guys!!!
    But, such talks are not tolerated by the government, so be strong.
    you may be victimized…..

  2. ሶዶ ወራ ኬኛ

    እንኳን በሠላም መጣችሁ! ገዢዉ ግንባር የህትመት ሚዲያን ሙሉ ለሙሉ በምባል መልኩ ዘግቶ ገዘጠኞችን አስሯል ወይም ከአገር አባሯል። ምናልባት እናንተም ተመሳሳይ እጣ ልገጥማችሁ ይችላል የገዢዉ ቃለአቀባይ ካልሆናችሁ። ለማንኛዉም የምታይ ይሆናል በተቻላችሁ መጠን ሚዘናዊና ህዝባዊ ሁኑ። መልካም ዕድል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *