የሕግ ሰዎች፣ ሕግን ታደጓት!

 

ኅሊና ያለው ሰው ፈርቶ መኖርን አይተውም። ሌላውም ፈርቶት ኑሮውን እንዲተው አያደርግም። ባዶ እግሩን ሲሄድም ክንፍ አውጥቶ ሲበርም – ሰው ነውና ሁሌም የሆነውን ሆና እንጂ – ለአንዱ ሌላኛውን ‹‹አይገድልም››። ለራሱ ድሎት፣ ከሌለው ሥር ምድር እንደ ምንጣፍ ተጠቅልላ እንድትነሣ አያሤርም፣ አይሠራም።

ኅሊና ያለው ሰው – ሕግና ማስፈጸሚያ ስላለው እሺታውም እምቢታውም፣ ፍቅሩም ጥሉም፣ ጥላቻውም ስምምነቱም፣ ጦርነቱም መልክ አለው – ያምራል። ቢያንስ ይታያልና – ይታወቃል። ኅሊና ያለውን ሰው ሕልውና ማንም መካድ አይችልም።

የሕግ ባለሙያነት በልምምድ የሆነን ሥራ መሥራት መቻል ብቻ አይደለም። የሕግ ባለሙያነት ባሕርይና ስብዕና መፍጠር ነው። በዚህ ባሕርይ ለዚህ ባሕርይ መሆኛ የሚመች አካባቢ ለመፍጠር መሥራትና መኖር ማለት ነው። ስለሆነም፣ የሕግ ባለሙያው ያንን ለማጥፋት በመተባበር፣ የራሱን ስብዕና አያጠፋም። የፍርድ ቤትን ነፃነት እና ገለልተኝነት፣ የሕግ የበላይነትን እና የዜጎችን መብትና ነጻነት እንዳይከበር መሥራት እና ለዚያ ከሚሠራ አካል ጋር መተባበር፣ ያንን ለማጥፋት መሥራትና ከሚያጠፋው ጋር መተባበር ነውና።

ለሕዝብ መብት፣ ነጻነት እና እኩልነት መከበር መቆምን በባለሙያው ላይ በግዴታነት ያላስቀመጠ፣ ስብዕናውን ያልፈጠረበት፣ ለሕግ የበላይነት ያልቆመ የሕግ ባለሙያ፣ ከቶም ለሀገር አይጠቅምም።

የሕግ ባለሙያ፣ ለሚሠራባት ሀገሩ የሕግ ሥርዓት ጠበቃ፣ ዐቃቤ ሕግ ሆኖ ካልቆመላት – ራሱንና ሀገሩን እንደ ከዳ፣ ሙያውንም እንዳዋረዳት ይቆጠራል። አንድ የሕግ ባለሙያ፣ የሕግን ፍትሕ ላሹ ዜጎች ካቆመ፣ ለማንም ሊቆም አይችልም። ለፍትሕ ሥርዓቱ ሁሉንም በእኩል ዐይን መመልከት ዋነኛው አላባ – ይሄው የሕግ ባለሙያ ነው። ሕግም ሕግ የምትሆነው፣ ሕጓን ለታለመላት ዓላማ ሲያውሏ ነው።

እኛም እንላለን፡- ሕግ፣ ሕግ የምትሆነው፣ የሕግ ሰዎች ለሕግ ሲቆሙ ነው! ለሕዝብ ሲቆሙ ነው! የሕግን ልዕልና – በልእልናቸው ሲያስጠብቋት ነው!

About the author

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *