• ቃለ-ምልልስ – ጋዜጠኛ ጸደይ ለማ /የ‹‹አዲስ ስታንዳርድ›› መጽሄት ዋና አዘጋጅ/

  ‹‹ሀሳብ ስጋት የሆነበት መንግስት ሀገር መምራት አይችልም›› ‹‹መንግስት ሀሳብን ፈርቶ መኖር አይችልም›› ‹‹ሕገ-መንግስቱን ሳያከብር ‹መንግስት ሆኜ እቀጥላለሁ› ካለ የዋህነት ነው›› ጋዜጠኛ ጸደይ ለማ /የ‹‹አዲስ ስታንዳርድ›› መጽሄት ዋና አዘጋጅ/ ወደጋዜጠኝነት ሞያ ከተቀላለቀች 16 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የመጀመሪያው የእንግሊዘኛ ጋዜጣ በሆነችው ‹‹አዲስ ትሪቡን›› ላይ ጋዜጠኝነትን አንድ ብላ ጀመረች፡፡ ‹‹ኢንተርፕርነር›› እና ‹‹ዴይሊ ሞኒተር›› በተሰኙ እንግሊዘኛ ጋዜጦች ላይም ሰርታለች – […]

 • ጤና – ፓርኪንሰን

  ትዕግስት ታደለ የሰው ልጅ ኑሮውን ለማቅለል በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በርካታ ምርምሮችን ቢያደርግም በሚያደርገው ምርምር የተነሳ የሚመጡበት የጎንዮሽ ጉዳቶች በርካታ ናቸው፡፡ በተለይ ከዚሁ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ሥራው ጋር በተያያዘ በራሱ በሰው ልጅ የሚፈጠሩ በጤናችን ላይ ጉዳት የሚያደርሱ የበሽታ አይነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ ይገኛል፡፡ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ጋር በተያያዘ ሊከሰቱ ይችላሉ ተብሎ ከሚታሰቡ በሽታዎች ውስጥ […]

 • የቤተክርስቲያኒቱ የቀውስ ምንጭ – የፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት

  ተስፋዬ አ. tes983398@gmail.com እንደ መነሻ ከጥቂት ቀናት በፊት የደቡብ አፍሪካ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (SABC) በዜና ሰዓቱ በርካታ ሰዎችን ያሳተፈ እጅግ አስደንጋጭ የአንድ እናት ልጆችን ድብድብ ይዞ ለህዝብ ቀረበ፡፡ ይህ የወንድማማቾች ፀብ በእግር ኳስ አሊያም በቦክስ ግጥሚያ ሜዳ ወይም በምሽት ክበብ እንዳይመስላችሁ፤ የፀቡ ምክንያትም አደንዛዥ ዕፅ ወይም መጠጥ አይደለም፤ የፀቡ ተዋንያኖችም ዞምቢዎቹ ደቡብ አፍሪካውያን ወይም ደግሞ ሰዋዊ […]

 • የአምስት ዓመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን – ሚራዥ

  ጽጌረዳ ጎንፋ የበረሃ ተጓዥ ግመል ጎታች፣ ከሩቅቅቅ የሚታይ፣ በፀሐይ ኃይል አንፀባራቂ ሃይቅ መሳይ፤ የሚያጥበረብር አታላይ ምስል፤ የዓይን ላይ ጨዋታ ይገጥመዋል …ነገሩን ያለመደው እንግዳ መንገደኛ ታዲያ ውሃ አገኘሁ ብሎ ሲጓዝ ሲጓዝ ሲደርስበት ሲርቀው …ሲጠጋው ሲሸሸው …ምላሱ ከትናጋው በውሃ ጥም እስክትጣበቅ ሲያለከልክ የማይደርስበት …“እዛ ስደርስ ውሃ አገኛለሁ ከጥሜም እረካለሁ …አሸዋ የሸፈነው …መንገድ ያደከመው እግሬን ተለቃልቄ አርፋለሁ ..እረሰርሳለሁ” […]

 • ተሸበርኩ ባይ አሸባሪ!

  ተማም አባቡልጉ እንኳን አደረሳችሁ! የዘንድሮውን የድል በዓል ልዩ የሚያደርገው አርበኞች አባቶቼን በጦር፣ በጎራዴ …ወዘተ የኢጣሊያንን ፋሽስት ቅኝ ገዢ መንግስት ለአምስት አመታት በዱር በገደሉ ተዋድቀው ድል በመምታት ለሁለተኛ ጊዜ አሳፍረው ከሀገር በመባረር ያስረከቡን ነፃነት እኛ ልጆቻቸው በ21ኛው ክፍለዘመን ዳር ድንበራችንን መጠበቅ አቅቶን ውድቅዳቂ መሣሪያ የታጠቁ የደቡብ ሱዳን ጎሳዎች ድንበራችንን ዘልቀው ገብተው ያሻቸውን መጠን ዜጎቻችን ገድለው፣ አቁስለውና […]

 • ሊነጋ ሲል ከቶም አይጭልምም!

  ቴዎድሮስ ጸጋ ሀገራችን ከገባችበት ውርደትና ዝቅጠት ነጻ መውጫ ሰዓቷ ደርሷል። ለእኔ፣ ሊነጋ ሲል አይጨልምም፤ ዐይኔ ከቶም ጥቁሩን ድቅድቅ ጭልማ ለማየት አይፈቅድም። ይልቅስ፣ ዐይኖቼ ከዋሻው ጫፍ ያለው ብርሃን ነው የሚታያቸው። ሊነጋ ሲል ያቅላላል ወጋገኑ፤ ወገግ ብሎ ይታያል። ይህንን የምለው የሰነፍ ግብዝነት ይዞኝ አይደለም። የዘመን አቻዎቼን ሩቅ ሕልም፣ በግፍ በየወህኒው የተጣሉ እውነት ናፋቂ ብርቱ ድምፆች፣ የሀገሬ አርሶ […]

 • ቃለ-ምልልስ – ሶሊያና ሽመልስ

  ‹‹ጭቆና እስካለ ድረስ የመብት ጥያቄዎችመልካቸውን እየቀያየሩ መምጣታቸው አይቀርም›› ‹‹አገራዊ ጭቆናው በጠነከረ ቁጥር ፕሬሱ ከፊት ለፊት የመጀመሪያው ተመቺ ይሆናል›› ሶሊያና ሽመልስ (ጦማሪ) ለቃለ-ምልልሱ ፈቃደኛ በመሆንሽ እናመሰግናለን፡፡ እኔም አመሰግናለሁ፡፡ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሦስት ጋዜጠኞች ከመታሰራቸው በፊት፣ ሲታሰሩ፣ በእስር ላይ እያሉ፣ ከእስር ከተፈቱ በኋላ የነበረሽን ስሜት እንዴት ትገልጪያቸዋለሽ? ያው እስሩ የተጠበቀም ቢሆን፤ በጣም አስደንጋጭ ነበር። ምንም ያህል […]

 • ህዝቤ ሆይ ተነሳ!

  ሰላማዊት አበበ venesiak@gmail.com ያለነው የነጻነት ሀገር፤ ግን እንቅስቃሴያችን የተገደበ፡፡ ያለነው የሰላማዊ ሀገር፤ ግን ውስጣችን ብጥብጥ እና ጦርነት! ያለነው በምንኖርበት አለም፤ በገሀድ የምንኖረው ደግሞ የማንኖርበትንና ያልተጻፈበትን የቅዠት አለም፡፡ ሀብታም ሲኖር ድሃ ሲያኗኑር መመልከት፡፡ በጣም ነው የሚገርመኝ! የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን ያልተመቻቸና የሚጎረብጥ የኑሮ ዘይቤን አሜን ብሎ ከተቀበለ ውሎ አድሯል፡፡ አይናገር ነገር ከፊቱ የሚጠብቀውን የጨለማ ኑሮ ይፈራል፡፡ (ለነገሩ […]

 • አፍሪካዊነት vs አውሮፓዊነት — የሁለት ባሕሎች ግጭት!

  በዮሴፍ ሙሉጌታ ባባ (ዶ/ር) kankokunmalimaali@gmail.com ክፍል 7 (ማስታወሻ፡- በዚህ እትም ላይ፣ አውሮፓዊያንና አውሮ-አፍሪካዊን ጠበብት በቅጡ ያልተረዱትን፣ በ“ፍልስፍና”ና በ“የፍልስፍና ታሪክ” መካካል ያለውን ልዩነት ለማቅረብ ቃል የገባው ቢሆንም፣ በሦስት አንኳር አንኳር ምክንያቶች ላልተወሰነ ጊዜ ለማቆየት ወስኛለሁ፤ (1ኛ) የፍልስፍና ታሪክም ሆነ ምንነትን በተመለከተ፣ እስከ አሁን የተደረሱት የምርምር ሥራዎች ብዛት ስላላቸው፣ ከስፋቱ አንፃር አንባቢው በጥልቀት አንብቦ በሂደት ቢረዳ የተሻለ […]

 • የዘውግ አከላለል የመፍትሄ ሐሳብ ሊሆን አይችልም! (ለፕ/ር መሳይ ከበደ ጽሑፍ መልስ)

  ግርማ ካሳ በእትም አሥር፣ አዲስ ገጽ፣ በዴተን ኦሃዮ የፍልስፍና አስተማሪ የሆኑት፣ መሳይ ከበደ (ፕ/ር) ‹‹የኢትዮጵያ ዘዉጋዊ ክፍፍሎችና የመፍትሄ ሐሳብ›› በሚል ርዕስ የጻፉትን አስነብባናለች። ጽሑፉ ሶስት ክፍሎችን ያካተተች ናት። የመጀመሪያው ክፍል ስለዘውግ (ethnicity) አንዳንድ ጽንሰ ሃሳቦች ለማሳየት ሞክሯል። ብዙም የማያከራክር ለጠቅላላ እውቀት የሚሆን ፍልስፍናዊና ቴዎረቲካል ትንተና በመሆኑ እዚያ ላይ ብዙ ጊዜ አላጠፋም። ሁለተኛው ክፍል፤ በሀገራችን ስላለው […]