• ወደፊት ለመሄድ፣ ትንሽ ወደኋላ…

  ዮሐንስ ሞላ ከነሙሉ ድክመቱም፣ በኢትዮጵያዊነቴ ኩሩ ነኝ። ‹ኢትዮጵያዊ ባልሆን ኖሮ የአድዋን ጦርነት ታሪክ ስሰማና ሳስብ ምን ሊሰማኝ ይችል ነበር?› ብዬ ራሴን ጠይቄ አውቃለሁ። ‹አረረም፣ መረረም› ደንቆኝም አላባራ ነበር። በተለያዩ የኑሮና የወዳጅነት አጋጣሚዎች ካገኘኋቸው የውጭ ሀገር ዜጎች ጋር ስለአድዋ ጦርነትና ድል ከተነሣ እኔም አውርቼ፣ እነሱም ተገርመው አናባራም። ስለላሊበላ ሲወራም እንዲሁ ነን። አማኝ ኢ-አማኝነታቸውን ወደ ጎን ተወት […]

 • የኢትዮጵያ ሴቶች የዘመኑ ጥያቄ ምንድን ነው?

  በሲቲና ኑሪ እና በዘላለም ክብረት   እመቤት የ50 ዓመት ኢትዮጵያዊ ስትሆን፤ የአምስት ልጆች እናትም ነች፡፡ የመጀመሪያ ልጇን የወለደችው በ20 ዓመቷ ሲሆን፤ ዛሬ ላይ ሁና ያሳለፈችውን ጊዜዋን መለስ ብላ ስታስበው ብዙ ትዝታዎች ከፊቷ ይመጡባታል፡፡ በቅርቡ በሞት የተለያት ባለቤቷ ያለእሷ ፈቃድ ከቤተሰቦቿ ጋር በመስማማት ብቻ ያገባት ሲሆን፣ ሶስት አስርትን ባስቆጠረው ትዳራቸው ውስጥ አንዴ ‹ወጥ አሳረርሽ› እያለ፣ ሌላ […]

 • መሬታውያን ትዝብት

  ቴዎድሮስ ዘውአለ ወደ ራስህ መመለስ፤ በራስህ ማንነት ውስጥ መኖር፤ እራስን መሆን፤ የማንነትን ቀውስ መከላከል። የቋንቋ ጥገኛ መሆን። አሁን ያለው የአእምሮአዊ ኹነት፣ ግንዛቤ እንዲሁም ይህን ተከትሎ የመጣው ምርጫ፣ አእምሮ/ኣዊ/ ምልሰት እና የአእምሮ/ኣዊ/ ትኩረት መሰብሰቡ ንቃት ለሚያስፈልጋችሁ እህቶችና ወንድሞች እንዲሁም ወላጆች በሙሉ ትዝብቴን ከመጀመሬ በፈት ምስጋና፣ ክብር ለልዑል (ለአሸናፊው አባት)፤ ለአእምሮ(አዊያን) ፍጡር፤ ለልዑል መላዕክትን ለአካላ(ዊያን) ፍጡር (ለመላዕክታን) […]

 • ብርሌ ከነቃ አይሆንም ዕቃ

  ተማም አባቡልጉ ኢህአዴግ በኦሮሚያ ክልል ለተፈፀመው የጦር ወንጀል (ቶርቸርና በአደባባይ ሰውን መረሸን ተጠያቂ የሚሆኑ የጦርና የሲቪል ባልሥልጣናቱን ለፍርድ የማቅረብ ፍላጎትና ፍቃደኝነት የሌለውና የወንድሞቻችን፣ የእህቶቻችን፣ የልጆቻችን፣ የእናቶቻችንና የአባቶቻችን ደም እንደውሻ ደም እንዲሁ በአደባባይ ፈስሶ ሊቀር ለመሆኑ ማረጋገጫ ባለሥልጣናቱ ሰሞኑን ስለዚሁ ጉዳይ በሚሰጡት ቃል የማጣራቱን ሂደት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እየፈፀመ ነው ማለታቸው ነው፡፡ በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ የቱንም […]

 • ‹‹ያቤፅ››!

  ቴዎድሮስ ጸጋ ያቤፅ ይባላል፤ ተወልዶ ያደገዉ ፒያሳ ደጃች ዉቤ ሰፈር ሲሆን ወላጅ እናቱ ያለአሳዳጊ አባት፤ አረቄ እየቸበቸቡ ነበር በመከራ ያሳደጉት፡፡ እቅዱ ትምህርቱን ጨርሶ እንደተመረቀ ወደ ስራዉ አለም ተቀላቅሎ እናቱን ማገዝ ነበር! ይሄዉ ዕቅዱ እንዲሰምርለትም ሊመረቅ አንድ አመት ሲቀረዉ የገዢዉ ፓርቲ አባል እንዲሆን ሲጠየቅ ሳያቅማማ ወዲያዉኑ ነበር እሽታዉን የገለፀላቸዉና አባል የሆነዉ፡፡ ፖለቲካን ባያዉቅም፤ ከስራ ገበታ ጎድሎ […]

 • ስፖርት

  ፍርድያውቃል ንጉሴ firdyawkal@gmail.com   መፍትሔዎቹ… ባለፉት ሁለት እትሞች ላይ በሚዲያዎቻችን ዘንድ የሚቀርቡት የስፖርት ፕሮግራሞች ላይ ስለ እግር ኳስ ብቻ መወራቱና ሌሎች ስፖርቶች ከነጭራሹ መረሳታቸው ያለውን ተግዳሮትና አሳሳቢነቱን ለመግለፅ ሞክሬያለሁ፡፡ በቀጠሮዬ መሰረት በዚህ ሳምንት ደግሞ ይህ የተበላሸ አካሔድን ማስተካከል የሚቻልባቸውን የመፍትሔ ሀሳቦች እንደሚከተለው ዳስሻለሁ፡፡ የስፖርት ኮሚሽኑ ሃላፊነት በሀገራችን ያሉ ሁሉም የስፖርት አይነቶች ያድጉና ይጎመሩ ዘንድ ትልቅ […]

 • ባርነት፣ በአዲስ ሰንሰለት

  አብርሃም ፈቃደ እስኪ አሁን እኛ የኢትዮጵያ ህዝብ አርነት አለን ሊባል ነውን? አርነት ያለው ህዝብ ማለት እውነተኛ ትርጉሙ ለብቻው መንግስት ያለው ህዝብ ማለት ብቻ አይደለም፡፡ እራሱን የቻለ ሕዝብ ማለት ነው እንጂ ይሉናል ነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ ከ92 ዓመታት በፊት በከተቡት መጽሐፍ ውስጥ፡፡ በዕድሜ ለአንቱታ ያልበቁት በእውቀት ደግሞ ለአንቱታ ክብር የተገቡት ወጣቱ ነጋድራስ ገ/ህይወት ‹‹ሰዎች መንግስት ስላላቸው በአርነት […]

 • ‹‹ፔጅ›› ጥቆማ

  ኤርሚያሰ የሺጥላ   ቀኑ ደመናማ ወይም ከፊል ደመናማ ነው ብዬ አልጀምርም። ምክንያቱም ‹‹ቀኑ ደመናማ ነው›› ብሎ መጀመር የኢትዮጵያ ደራሲያን ሙዳቸው ነው ስልተባለ ብቻ ሳይሆን፣ ቀኑን አላየሁትም፤ እቤት አልጋዬ ላይ ተኝቼ ነው ያለሁት። እኔ የምኖርበት ቤት ደግሞ የተሰራው በፈረንሳይ አርክቴክት የጥበብ ሐሳብ ሳይሆን፣ በአበሻ ቤት አከራይ ፍላጎት ስለሆነ፤ የእግዚአብሔርን ፀሐይ አይደለም የአከራዬን ልጅ ጀንበርን ስትወጣ ስትገባ […]

 • የቋንቋ አስተናባሪዎች አደገኛው መንገድ

  በነገሠ ተፈረደኝ   ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋ ነበረች። ከምስራቅም ተነስተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፣ በዚያም ተቀመጡ። እርስ በርሳቸውም ‹‹ኑ ጡብ እንስራ፣ በእሳትም እንተኩሰው›› ተባባሉ፣ ጡቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው፤ …  ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንስራ፤ በምድር ላይ ሳንበተንም ስማችንን እናስጠራው›› አሉ። እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሰሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። […]

 • ያለፈውን ትውልድ ነቃፊ …ማርጀት ወንጀል ነው?

  ነፃነት በለጠ Shawel_negash@yahoo.com ሙጋቤ ግን ዕድሜያቸውን በትግል ጀምረው በትግል ለመጨረስ የወሰኑ ታላቅ የአፍሪካ ልጅ ናቸው፡፡ የዕድሜን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ትግላቸውን (package) ማየት አስፈላጊ ስለሆነ ነው፡፡ በቅርቡም ይለይላችሁ ብለው የ92 ዓመት ልደታቸውን አክብረዋል፡፡   በእርግጥ ስኬት ያለተተኪ ውድቀት ነው ”Success without successor is failure –Maxwell” ይባላል፡፡ የአፍሪካ መሪዎች ሥነ ልቦና ‹እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል› ነው፡፡ ስለሆነም […]