• ኦሮሚያ በልጆቿ አሟሟት ደም አለቀሰች! (ኦሮሚያ ዱኣ ኢጆሌሼን ኢገ ቦሴ!)

    ሀብታሙ ምናለ የህዝቡንና ወገኑን ግፍ እና መከራ ብሎም የሚደርሰውን ሰቆቃ  እንዳላየ፣ እየሰማ እንዳልሰማ  በመሆን ኢትዮጵያዊነቱን እርግፍ አድርጎ ትቶ ቀንም ሆነ ማታ አሳቡና አዳሩ፡- ጀርመን ውስጥ ስለሚደረገው አፈና ፤ ፈረንሳይ ውስጥ ስለተደረገው ግድያ፤ አሜሪካ ውስጥ ስለደረሰው ፍንዳታ የሆነበት፣ ከማዘን አልፎም  ዳስ ጥሎ ለቅሶ መቀመጥ የሚቃጣው  አለ፡፡ ምክንያቱም ለእሱ ሰው ማለት በውጭ ያለ ባዕድ ነው፡፡ እዚህችው ሀገሩ […]

  • መልካም አስተዳደር መለኪያው ምንድነው?

    ነፃነት በለጠ   Email: <Shawel_negash@yahoo.com>   ይህ ቃል በአሁኑ ወቅት የሁላችንም ማለትም (የመንግሥትም የኅብረተሰቡም) አጀንዳ እንደሆነ እገምታለሁ፡፡ መልካም አስተዳደር (Good Governance) የመሰልጠንና ያለመሰልጠን ወይም የደም/የዘር ቀለም ጉዳይ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ የአስተሳሰብና የአመለካክት (World View/Attitudes) ውጤት ነው ማለት ይቻላል፡፡ አንድ ጸሐፊ እንዲህ ብሏል፡- “Bad governance is being increasingly regarded as one of the root causes […]

  • ወንድም እህቶቻችን የት አሉ?

    ግርማ ካሳ   ሁለት ወንድማማቾች ናቸው። ቃየን እና አቤል ይባላሉ። በዘፍጥረት ውስጥ፣ ‹‹ቃየን ወንድሙን አቤልን – ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየን በወንድሙ አቤል ላይ ተነሣበት፣ ገደለውም፡፡›› ይለናል (ዘፍ. ምዕ. 4፤ ቁ. 8) ደም ፈሰሰ። የወንድም ደም በወንድም እጅ። እግዚአብሔር በሆነው ነገር አዘነ። ለቃየንም ጥያቄ አቀረበለት፤ ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?›› አለው። ቃየንም መለስ፤ […]

  • አድዋን የማስረሣት አባዜ

    ፍቃዱ በቀለ fbekele23@gmail.com   በተለያየ ጊዜያት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ሕይወታቸውን ሳይሰስቱ – ‹የእኔ በሕይወት መኖር ከወገኔ ክብር አይበልጥም›› ብለው – ሕይወታቸውን ሰጥተውላታል፤ ወሳኝ በተባሉ ጊዜያት ፈጥነው ደርሰውላታል፤ ክፉ ፈተና ከፊታቸው ተደቅኖባቸው እንኳ በአስደናቂ ቁርጠኝነት ለሀገራቸው ጉዳይ – ካለምንም ቅድመ ሁኔታ – ሕይወታቸውን ሰጥተው እዚህ አድርሰዋታል፤ እነርሱም ስማቸውን ከመቃብር በላይ አኑረዋል። የተከበሩ የዓለም ሎሬት ጸጋዬ […]

  • ሴቶቻችን ሆይ፣ አደባባዩ ላይ በተግባር ተገኙ! ‹‹አደባባዩ›› ካለናንተ አያምርምና!

    ኤልያስ ገብሩ   ሴት ልጅ እናት ናት – ታላላቅ ጀግኖችን የወለደች! ሴት ልጅ ሚስት ናት – ታላላቅ ነገሥታትን፣ መሪዎችን፣ ባለሙያዎችን፣ ግለሰቦችን ከጎንና ከጀርባ ሆና ለስኬት ያበቃች! ሴት ልጅ እህትም ናት – ለወንድም ብልህ-መካሪና ባለውለታ! ስለሴት ልጅ ብዙ ነገር መዘርዘር ይቻላል። ዘርዝሮ መጨረስ አይቻልምና፣ በዚህ መጣጥፌ ሴቶች ከሀገራችን ፖለቲካ አውድ አኳያ ያላቸውን ድርሻ በአጭሩ ለማየት ወደድኩ። […]

  • የኛ ኦማር አፊፊዎች የት ናቸው?

    በላይ ማናዬ ኦማር አፊፊ በለበሰው የፖሊስ የደንብ ልብስ ኩራት ይሰማዋል፤ ፖሊስነቱን ይወደዋል፡፡ በተለይ በሚከፈለው ደመወዝ እና በደህንነቱ ምክንያት ስራውን አብዝቶ ይፈልገው ነበር፡፡ ኦማር አፊፊ ግብጻዊ ሲሆን እ.አ.አ በ1981 (ልክ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ወደ ሥልጣን ሲመጣ) በ16 አመቱ ወደ ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም ገባ፡፡ ኦማር በፖሊስነት ስራው ለማኅበረሰቡ አንዳች ነገር እንደሚያበረክት አምኗል፡፡ ሆኖም ወጣቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የደንብ […]

  • ርዕስ የለውም ርዕስ የለውም ርዕስ የለውም

    በቃሉ አጥናፉ ታዬ (ዶ/ር) (bekaluatnafu@yahoo.com)   በመጽሐፍ ቅዱስ በሉቃስ ወንጌል ላይ አንድ ታላቅ መልዕክት እንዲህ ይነበባል፤ አንድ የሕግ አዋቂ ራሱን ሊያፀድቅ ወድዶ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን፣ “ባልንጀራዬስ ማን ነው?” አለ። ኢየሱስም እንደሚከተለው በምሳሌ አስረዳው። “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ። እነርሱም ደግሞ ገፋፉት፣ ደበደቡትም በህይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ። ድንገትም አንድ ካህን […]

  • የመቶ ቀናቱ የአደባባይ ተቃውሞ

    በፍቃዱ ኃይሉ   ማክሰኞ (የካቲት 29፣ 2008)፤ ከጠዋቱ 2፡30 ላይ የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ፕሮጀክት (ኢሰመፕ) የተባለ ተቋም ‘Oromo Protests – 100 Days of Public Protest’ (የ100 ቀናት የኦሮሞዎች የአደባባይ ተቃውሞ) የሚል ሪፖርት አውጥቶ ነበር። ሪፖርቱን ከበይነመረብ ላይ አውርጄ ስልኬ ላይ እያነበብኩ ወደ ሽሮሜዳ ሄድኩ። አካሄዴ የቀጠርኩትን ሰው ለማግኘት ነበር። ሰዐቱ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ገደማ ነው። […]

  • ቃለ-ምልልስ – አቶ አስራት

    ‹‹መንግሥትም ሆነ ሕዝብ በተቀሰቀሰው አመጽ ሊገረምና ሊደነግጥ አይገባውም!›› ‹‹በወቅቱ የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ምንም የፓርቲ ፖለቲካ ሊሰራ አይችልም›› የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳሉ ጀምሮ ነበር የፖለቲካ ተሳትፎ የጀመሩት፡፡ በቀድሞ መንግስት ትምህርት ሚኒስትር ውስጥ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሰርተዋል፡፡ በፓርቲ ፖለቲካም በኢዴፓ፣ ቅንጅትና የቀድሞ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ስራዎች ላይ ንቁ […]

  • ‹‹ኦሮሞ ጀግና ነው!››

    አናንያ ሶሪ   ‹‹ኦሮሞ ጀግና ነው!›› ማለት፡- እንደ ሕዝብ መገለጫው የሆነውን ገዢ ባህርይ መናገርና ማወጅ ነው፡፡ ለዘመናት በብዙ ፈተናና ዕድሎች ውስጥ ያለፈው ይህ ትልቅ ሕዝብ የገድሉን ያህልም ያልተነገረለት ነው፡፡ ዛሬ በዚህ ጽሁፍ፡- በግሌ ለዓመታት ከነበሩኝ ዕይታዎችና አስተውሎቶች ተነስቼ ይህን ድንቅ ሕዝብ ለማመስገን ለመዘከር እና ለማወደስ ወደድኩ… ቢቻለኝም፡- በተከታታይ በአገራችን ስለሚገኙ ማሕበረሰቦች መጻፌን እቀጥላለሁ፡፡ ነገር ግን፡- […]