‹‹አሁን ሕዝቡ ሙሉ በሙሉ በመንግስት በጎ ፍቃደኝነት ስር ወድቋል››
አቶ አምኃ መኮንን /የህግ ባለሙያ/ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡ መቀመጫውን እንግሊዝ ሀገር ባደረገው ‹‹ኤሴክስ›› ዩኒቨርሲቲ በዓለም-ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ሰርተዋል፡፡ እንደዛሬው በጥብቅና እና በሕግ አማካሪነት ከመሰማራታቸው በፊት በፍትሕ ሚኒስቴር ውስጥ ለበርካታ ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪነትም በግል ዩኒቨርሲቲዎች አስተምረዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ የተከሰሱ እና እየተከሰሱ ለሚገኙ ሰዎች ጠበቃ በመሆን […]