• የአዲስ ገጽ መጽሄት ህትመት ተቋረጠ

  የአዲስ ገጽ መጽሄት ህትመት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ቆሟል:: ሁኔታዎች ፈቅደው ወደገበያ እስክንመለስ ድረስ እስካሁን አብራችሁን ለነበራችሁ ሁሉ ምስጋናችን ከልብ ነው::

 • ለእያንዳንዱ ያነበባችሁት ጽሁፍ ሃሳባችሁን ስጡን

  ለተከበራችሁ የአዲስ ገጽ መጽሄት ደንበኞች: በርካታ አንባቢዎች ድረ-ገጻችንን http://www.addisgets.com/ እየጎበኛችሁና እያነበባችሁ እንደሆነ እናውቃለን:: በድረ-ገጹ ላይ የመጽሄቱን ጽሁፎች የምናሰቀምጥበት ምክንያት በተቻለ መጠን ብዙ ወገኖቻችን እንዲያነቡት በማሰብ  ነው::  በድረ-ገጹ ላይ ያነበባችሁትንና የወደዳችሁትን ጽሁፍ እግረመንገዳችሁን ከእያንዳንዱ ጽሁፍ ስር ባለው የአስተያየት መስጫ ቦታ ሃሳባችሁን ብታስቀምጡ ለጻፉት ሰዎች ማበረታቻና ለሌሎች ወገኖችም ሃሳባችሁን ማካፈያ መንገድ ይሆናል::  በተጨማሪ እዛው ከእያንዳንዱ ጽሁፍ አጠገብ […]

 • የአዲስ ገጽ መጽሄት ድረ-ገጽ ቀጣይ ዕትሞችን እንደወጡ በኢንተርኔት በቀላሉ ለማንበብ እንዲያስችል ተደርጎ ተሻሻለ::

  ለውድ የአዲስ ገጽ መጽሄይ ደንበኞች የአዲስ ገጽ መጽሄትን በኮምፒዩተራቸሁ ላይ አዲስ አበባ ካሉት ወገኖቻችን እኩል ለማግኘት በድረ-ገጻችን http://www.addisgets.com/ “የዕትሞች ቋት” ውስጥ ገብታችሁ እያንዳንዱን ጽሁፎች እየመረጣችሁ ማንበብ ትችላላችሁ:: የተሰራው የክፍያ ሲስተም ስራ እስኪጀምር ድረስ ከታች የተዘረዘሩትን ለሙከራ የተዘጋጁ መረጃዎች በመጠቀም ማንበብ ትችላላችሁ:: የክፍያ ሲስተሙ ስራ ሲጀምር በተመጣጣኝ ክፍያ ማንበብ ይቻላል:: Test Mode Steps 1. Go to […]

 • የአዲስ ገጽ መጽሄትን በኢንተርኔት ያንብቡ::

  ለውድ የአዲስ ገጽ መጽሄት ደንበኞች: የአዲስ ገጽ መጽሄት 6ኛ ዕትምን ጨምሮ የቀደሙ ዕትሞችን ከመጽሄቷ ድረ-ገጽ “www.addisgets.com” “የዕትሞች ቋት” ውስጥ በመግባት ማንበብ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን:: መልካም ንባብ!

 • የአዲስ ገጽ መጽሄት ስድስተኛ ዕትም ለንባብ በቃ::

  የተከበራችሁ የአዲስ ገጽ ደንበኞች: ምንም እንኳን ሙሉበሙሉ እየታገሉን ያሉ ችግሮችን መፍታት ባንችልም ቃላችንን ለመጠበቅ ያህል አዲስ ገጽ ተመልሳ መጥታለች:: በሂደት ሁሉም ተሰተካክሎ እነደምናይ ተስፋ እናደርጋለን:: ሌላው ነገር አዲስ ገጽ አሁን 13 ብር ሆናለች:: እንደምታውቁት በሀገራችን ባለው ሁኔታ የተነሳ ከሽያጭ ውጭ አዲስ ገጽ እራሷን የምትደጉምበት በቂ የማሰታወቂያ አማራጭ ለጊዜው የለም:: ድርጅቶችና ግለሰቦች መንግስታቸውንና ፖለቲካን እንደ መብት […]

 • የአዲስ ገጽ መጽሄት ህትመት ለአንድ ሳምንት ሊቋረጥ ነው

  ለውድ የአዲስ ገጽ መጽሄት ደንበኞች:   የአዲስ ገጽ መጽሄትን የእስከአሁን የህትመትና ስርጭት ሂደት፣ የአንባቢያን አስተያየት፣ የዝግጅት ክፍሉን ኢመደበኛ የዳሰሳ ጥናት እና ተያያዠ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ በተሻለ ይዘትና ዝግጅት ለአንባቢያን ለማቅረብ እንዲሁም የታዩ ጉድለቶችን ለመሙላት ያስችል ዘንድ ለአንድ ሳምንት ህትመት ለማቋረጥ የዝግጅት ክፍሉ ወስኗል:: ስለሆነም አንባቢያን በኣሁኑ ቅዳሜ አዲስ ገጽ እንደማትኖርና ለሚቀጥለው ቅዳሜ ግን በተሻለ ሁኔታ […]

 • የአዲስ ገጽ መጽሄት 5ኛ ዕትም ቅዳሜ ጥር 7/2008 ዓም ለንባብ ትበቃለች::

  የተከበራችሁ የአዲስ ገጽ መጽሄት ደንበኞች: እንደተለመደው መጽሄታችሁ ነገ ቅዳሜ ጥር 7/2008 ዓም ለንባብ ትበቃለች:: በዚህ የአዲስ ገጽ 5ኛ ዕትም ላይ የተለያዩ ሀሳቦች ተንፀባርቀዋል:: መጽሄቷ አንድ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ጋብዛ ስለ ወቅታዊ ጉዳዮች ከጋዜጠኞቻችን በቀረቡላቸው ጠንካራና ትግስት የሚፈታተኑ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ ሰጥተዋል:: በአንፃሩ አንድ ታዋቂ የህግ ባለሙያ ጋብዛ ከህግ አግባብ ዕይታቸውን አስፍራለች:: የተለያዩ ፀሃፊዎች ከዚህ በፊት […]