ወደፊት ለመሄድ፣ ትንሽ ወደኋላ…
ዮሐንስ ሞላ ከነሙሉ ድክመቱም፣ በኢትዮጵያዊነቴ ኩሩ ነኝ። ‹ኢትዮጵያዊ ባልሆን ኖሮ የአድዋን ጦርነት ታሪክ ስሰማና ሳስብ ምን ሊሰማኝ ይችል ነበር?› ብዬ ራሴን ጠይቄ አውቃለሁ። ‹አረረም፣ መረረም› ደንቆኝም አላባራ ነበር። በተለያዩ የኑሮና የወዳጅነት አጋጣሚዎች ካገኘኋቸው የውጭ ሀገር ዜጎች ጋር ስለአድዋ ጦርነትና ድል ከተነሣ እኔም አውርቼ፣ እነሱም ተገርመው አናባራም። ስለላሊበላ ሲወራም እንዲሁ ነን። አማኝ ኢ-አማኝነታቸውን ወደ ጎን ተወት […]